የመንግስት አገልግሎቶችን ይበልጥ ቀልጣፋ ለማድረግ እና ትክክለኛ ማንነትን ለማረጋገጥ፤ ዚጎች ባለ 10 አሃዝ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥራቸውን (TiN) ከፋይዳ ዲጂታል መታወቂያቸው ጋር ማገናኘት ይጠበቅባቸዋል።
መታወቂያዎን እንዴት ማገናኘት ይችላሉ?
- በይፋዊው ድረ-ገጽ https://mor-migration.fayda.et/step/1 ላይ ይግቡ።
- በገቢዎች ቢሮ የተሰጠዎትን ባለ 10 አሃዝ የቲን (TiN) ቁጥር ያስገቡ።
- ሲጠየቁ ባለ 16 አሃዝ የፋይዳ መግቢያ ቁጥርዎን (FAN) ያስገቡ።
- የማረጋገጥ እና የማገናኘት ሂደቱን ለማጠናቀቅ በስክሪኑ ላይ የሚመጡትን መመሪያዎች ይከተሉ።
የፋይዳ መለያ ቁጥርዎን (FAN) የት ያገኙታል?
የፋይዳ መግቢያ ቁጥርዎ (FAN) በአቅራቢያዎ ከሌለ፣ በሚከተሉት መንገዶች ማግኘት ይችላሉ፦
- በእጅዎ ባለው የታተመው ወይም በኦንላይን የፋይዳ መታወቂያ ካርድዎ ላይ፣
- በይፋዊው የዲጂታል መታወቂያ (Digital ID) የሞባይል መተግበሪያ ላይ፣
- በቴሌብር (telebirr) መተግበሪያ ውስጥ፣
- መታወቂያውን ሲያስመዘግቡ በስልክዎ የደረሰዎት የመጀመሪያው የማረጋገጫ የአጭር የጽሑፍ መልዕክት (SMS) ላይ።

