ወለድ (Interest) ምንድን ነው?
ወለድ ማለት በአጭሩ “የገንዘብ ኪራይ” ማለት ነው።
- ለባንክ ገንዘብ ሲያበድሩ (ሲቆጥቡ)፦ ባንኩ የእርስዎን ገንዘብ ስለተጠቀመበት ለውለታው ተጨማሪ ገንዘብ ይከፍልዎታል፤ ይህ የቁጠባ ወለድ ይባላል።
- ከባንክ ገንዘብ ሲበደሩ፦ የባንኩን ገንዘብ ስለተጠቀሙ ተጨማሪ ክፍያ፤ ይከፍላሉ ይህ የብድር ወለድ ይባላል።
ቀደም ሲል በኢትዮጵያ የቁጠባ የወለድ መጠን የሚወሰነው በብሔራዊ ባንክ ነበር። ከጥር 2018 ጀምሮ ግን ባንኮች የወለድ መጠንን ራሳቸው እንዲወስኑ ነፃነት ተሰጥቷቸዋል።
ጥቅሙ፦ ባንኮች ደንበኛ ለማግኘት ይወዳደራሉ። አንዱ ባንክ 8% ወለድ ሲሰጥ፣ ሌላው 10% ሊሰጥ ይችላል። ስለዚህ ደንበኞች የተሻለ የሚከፍላቸውን ባንክ መምረጥ ይችላሉ።
2. የብድር ወለድ እንዴት ይቆጠራል?
አብዛኞቹ ባንኮች ቀሪ ላይ የሚታሰብ ወለድ (Declining Balance Method) ይጠቀማሉ ይህ ማለት ወለዱ የሚታሰበው ባልከፈሉት ቀሪ ገንዘብ ላይ ብቻ ነው።
ምሳሌ፦ 100,000 ብር ብድር ለአንድ ዓመት ወሰዱ እንበል። ዓመታዊ ወለዱ 15% ቢሆንና በየወሩ 9,025 ብር ለመክፈል ይስማማሉ፦
ደረጃ 1 (የመጀመሪያው ወር)፦ ወለድ = 100,000 ብር × (15% ÷ 12 ወር) = 1,250 ብር።
- ከከፈሉት 9,0150 ብር ውስጥ 1,250 ብር ለወለድ ሲውል፣ ቀሪው 7,775 ብር ዋናውን ብድር ይቀንሳል።
አሁን ያልተከፈለ ቀሪ ብድር = 92,224 ብር
- ደረጃ 2 (ሁለተኛው ወር)፦ አሁን ወለዱ የሚታሰበው በ92,224 ብር ላይ ነው።
ወለድ = 92,250 ብር × 1.25% = 1,152 ብር (ወለዱ ቀነሰ!)
በየወሩ በከፈሉ ቁጥር የዋናው ብድር መጠን ስለሚቀንስ የሚታሰበው ወለድም አብሮ እየቀነሰ ይሄዳል።
3. የቁጠባ ወለድ እንዴት ይሰላል?
ባንኮች ወለድ የሚሰጡት በወር ውስጥ ባለው “ዝቅተኛው የገንዘብ መጠን ወይም በቀን ውስጥ በቀረብ የገንዘብ መጠን ላይ ተመስርተው ነው።
ምሳሌ፦ በወር ውስጥ 50,000 ብር ነበረዎት እንበል አውጥተው አውጥተው ወሩ ከማለቁ በፊት ዝቅተኛው ቀሪ 10,000 ብር ቢሆን፣ ባንኩ ወለድ የሚሰጠው በ10,000 ብሩ ላይ ብቻ ነው።
4. ብድር ከመውሰዳችሁ በፊት እነዚህን አጣሩ
- ባንኮችን ያወዳድሩ፦ አሁን ባንኮች የራሳቸውን ወለድ ስለሚወስኑ ብድር ከመውሰድዎ ወይም ከመቆጠብዎ በፊት ቢያንስ 3 ባንኮችን ጠይቀው የተሻለውን ይምረጡ
- የወለድ አይነትን ይጠይቁ፦ ወለዱ የሚታሰበው በወሰድኩት ጠቅላላ ገንዘብ (Flat rate) ላይ ነው ወይስ በቀሪው (Declining) ላይ? ብለው መጠየቅዎን አይርሱ በቀሪው ላይ ሲሆን ለተበዳሪ ሁልጊዜ የተሻለ ነው።
ፋይናንስን ማወቅ ማለት ገንዘብን ማሸነፍ ነው። ወለድ እንዴት እንደሚሰላ ማወቅ የትኛው ባንክ እንደሚጠቅም ለመወሰን ይረዳል እንዲሁም የገንዘብ አጠቃቀምን ብልህ ያደርገዋል። ስለዚህ ዛሬውኑ ወደ ባንክዎ ጎራ ብለው ስለ አዲሱ የወለድ ተመን ይጠይቁ።

